23/09/24 :

    የባለአክሲዮኖች 11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ



    በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ16(1) መሠረት የቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል የሰብሰባ አደራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

    1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች

    1.1. የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 312፣ ዌብ ሳይት፡ www.bgmfi.com ፣ኢ-ሜይል፡ info@bgmif.com ፣ ፖስታ ሣ.ቁጥር፡ 24850 ኮድ 1000 ፣ ስልክ ቁ፡ +251-114-16-26-21

    1.2. የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፣ KK/AA/3/0001649/2004

    1.3. የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፣75,000,000 (ሰባ አምስት ሚሊዮን)

    1.4. የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፣10,000,000 (አስር ሚሊዮን)

    2. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

    2.1. የጉባዔዉን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣

    2.2. በ10ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአንቀጽ 6.3. ሥር የማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ የተላለፈውን ዉሳኔ መሻር፣

    2.3. የማህበሩን አክሲዮን ማስተላለፍ፣

    2.4. የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ እና የተከፈለውን ካፒታል ማሳወቅ፣ እና 2.5. የጠቅላላ ጉባኤውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ ናቸው።

    3. ማሳሰቢያ
    3.1. በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት በቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክሲዮን ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ በመሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

    3.2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባኤ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ብጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

    የቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ






    4/01/24 :
    BG will implement mobile point-of-sale (POS) systems for its credit and saving business within the coming one year. This newer Android POS System is mobile and user-friendly to work with smartphone or tablet. This means it can help to accept payments from anywhere. It includes tools to connect to main branch system online.